You are here: HomeSocial Issues ብሩህ ተስፋ ለሚታያት #ልባም ቤተክርስቲያን!

ብሩህ ተስፋ ለሚታያት #ልባም ቤተክርስቲያን!

Written by  Thursday, 16 May 2019 08:53

ኢትዮጵያ ካላት ጠቅላላው ሕዝብ ብዛት 70 በመቶ የሚያክለው እድሜቸው ከ 25 በታች የሆኑ እነደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡ ይህ ማለት 100 ሚሊየን ህዝብ ቢኖራት ከ70 ሚሊየን በላይ ወጣት ይኖራታል ማለት ፡፡ 70 ሚሊየን ዕድል ሐገርን ለመለወጥ በእጃችን አለ ማለት ነው ፡፡


ዓለማችን በፈጣን ለውጥ ላይ ትገኛለች


ታድያ የዓለማችንን የጊዜው አካሔድ ለማየት ከሞከርን አለም ከመቼውም ጊዜ በላይ በለውጥ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ፡፡ አንድ ሰው እንዳለው ዓለም እንደ ፈጣን ባቡር ነች ፣በፍጥነት እየበረረች ትገኛለች በየፌርማታው ብዙ ትውልዶችን ትጭናለች ፡፡ የንግድ ስርዓቱ፣የፖለቲካ ስርዓቱ እና የማህበራዊ ስርዓቱ ይህንን ትውልድ እንደ ዕድል የሚያዩ እና እድሉን ተጠቅመው ትውልድን የሚደርሱ የዚህ ዓለም አሰራሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ናቸው ፡፡


በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣቱን ትውልድ ማእከል ያደረጉ ንግድ ማስታወቂዎች በብዛት ይሰራሉ ለምሳሌ ያህል ወጣቶችን ወሲብን በማበረታታት ስታይልን ወይም ዘመናዊነትን ለልቅነት የሚዳርግ በዲኬቲ ኢትዮያ እየተዘጋጀ የሚቀርበው ስታይል የወሊድ መከላከያ ፣ የሐገርንና የህዝብን ክብር ፣ኢትዮጵያዊነትን እነዲሁም ታላቅ መሆንን ከርካሽ ቢራ ጋር እያያዘ ወጣቶችን ለአልኮል ሱስ የሚዳርገው የሐበሻ ቢራ ማስታወቂያ እንዲሁም ከሰሞኑ ብብዙ መነጋገሪያ እሆነ ያለው ከልባምነት፣አስተዋይነት እና አማኝነት ጋር ተያይዞ የተሰራው የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ ከብዙ በጥቂቱ ይገኙበታል ፡፡


ከላይ ያነሳኃቸው ማስታወቂዎች ለእኔ የሚያመለክቱኝ የዚህ ዓለም አምላክ ሆነው ዲያቢሎስ የትውልዱን ልብ ለማሳወር እና ትውልዱን ደቀ መዝሙር ለማድረግ ምን ያህል እየተጋ ነው የሚለውን ነው ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር በተቀበለችው ስልጣን (Mandate) እና ሐላፊነት ትውልዱን ከፊቱ የተጋፈጠውን ፈተና እና ተግዳሮት እነዲያመልጥ በክርስቶስ እየሱስ ወንጌል ወይም የምስራችን በመስበክ በዓለም ላይ የጨውና የብርሃን ሚናዋን በመወጣት ትውልዱን እያስመለጠች ነው ወይ ሚል ጥያቄንም ይጭርብኛል ፡፡


በመጨረሻም ከሰሞኑ አንዳንድ ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶች በዚህ ጉዳይ የሰጡትን አስተያየት የመከብር ቢሆንም ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር ግን አስተያየቱ እንደ ለትውልዱ የሚቆረቆር አንድ ዜጋ ካልወሰድነው በቀር መጽሐፍ ቅዱስ መቼም ቢሆን ኃጢአት እና አመጽ በፊርማ ማሰባሰብ/Petition/ ሊጠፋ እነደማይችል ይናገራል ፡፡


ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። 
ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ 
ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ 
ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
2ጢሞቲዎስ 3፡1-4


ካላይ ያነሳሁት ቃል እንደሚመክረው የኀጢአት መልክ እና መጠን እየጨመረ የሚመጣ እንጂ በእኛ ተቃዉሞ የሚቀንስ እንዳልሆነ መረዳት እንችላለን ፡፡


የቤተክርስቲያን የአሁን መልክ

እኔ ዘመኑዋን ቤተክርስቲያን መልክ ለመግለጽ በአንድ ወቅት ታላቅ አገልጋይ አባት የተጠቀሙትን ቃል ብጠቅስ እወዳለሁ ፡፡ የዚህ ዘመን ቤተክስቲያን እንደ ናስ ነች አሉ እኚህ አባት በመጽሐፍ ቅዱስ ዮናስ የሚባል አንድ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነብይ ነበር ይህ ሰው እግዚአብሔር ለምድረ ነነዌ መልእክትን እንዲያደርስ ተልኮ እርሱ ግን ወደ ተርሴስ ምድር እንደሔደ ቃሉ ይነግረናል ፡፡ ነብዩ እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ወደ ተርሴስ ኮብልሎ በሄደበት መርከብ ውስጥ ማእበል እነደተናሳና እርሱ ግን ያ ሁሉ ማዕበል በመርከቡ ሲሆን እና በውስጡ የነበሩትን በሙሉ ሲያስጨንቅ በመርከ በታችኛው ክፍል በካባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበር ይላል ፡፡


….ዮናስም በካባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበር ፡፡
ትንቢተ ዮናስ 1፡5


ስለሆነም ወዳጆቼ ይህንን ጽሁፍ መልእክቴ ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን አጥብቃ መረዳት ያለባት ነገር ትውልድን ከህንፃ፣ከመሬት፣ከክብር እና ከገንዘብ በላይ ቀዳሚ ትኩረተ አድርጋ እና ከተኛችበት ከባድ እንቅልፍ ነቅታ በምድር ላይ የፅድቅ ተጽዕኖን የሚያመጣ ትውልድን በማስነሳት ብርሃንነትን እና ጨውነትን በመልክ ሳይሆን በጣዕም ተገባራዊ አድርጋ በምንም የማይረታ ትውልድን መፍጠር እንጂ ለሁሉም ኃጢአት ፊርማ አሳባሳቢ መሆን አዋጪ መገነድ ነው ብዬ አላምንም ፡፡


ጨለማ በራሱ ትርጉም የሌሽ ነገር ሲሆን ትርጉም የሚያገኘው ብርሃን ሳይኖር ብቻ ነው ብርሃን ካለ ጨለማ መኖር /exist / ማድረግ አይችልም ፡፡the true meaning of darkness is the absence of light!

Read 3790 times Last modified on Thursday, 16 May 2019 09:26
Pastor Fitsum N.Demisse

Youth Pastor @ Bible Army International Church

Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 130 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.