‹‹ አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ቢረዳም›› እውነቱን አውቆ እርሙን ማውጣት፣ ማድረግ ያለበትንም አስተውሎ ማድረግ ይሻለዋል፡፡
የእኛ አገር ነገር አደናጋሪ፣ አሳሳቢ፣ አስጨናቂ፣ አጠያያቂ ከሆነ ሰነበተ፡፡ በአንድ ወገን ሲቃና በሌላ ወገን ይደረመሳል፣ ዛሬ በሰለ ሲባል አድሮ ቃሪያ ይሆናል፡፡ እፎይታ የሩቅ ህልም እየመሰለ ሄደ፡፡ ውጥረትና ሁካታ የወትሮ ልብስ ሆኑ፤ ጣርና ሲቃ አየሩን ሞሉት፡፡ ለምንድነው ይህ የሚሆነው? ምን ቢሆን ነው የሚስተካከለው? መቼ ነው ይህ አገር አደብ የሚገዛው? ብርቱ ጥያቄ ልቦናችንን ይገዘግዛል፡፡ እንደ አገር ሁ...