You are here: HomeSermonናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር -Narcissistic Personality disorder የዘመኗ ቤተክርስቲያን ተግዳሮት

ናርሲስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር -Narcissistic Personality disorder የዘመኗ ቤተክርስቲያን ተግዳሮት Featured

Written by  Wednesday, 22 December 2021 15:50
የስነ ልቦና ምሁራን ሰዎችን ከሚያጠቁ የስነ ልቦናና የማንነት ቀውስ በሽታዎች አንዱ ናርስሲዝም የሚባል በሽታ መሆኑን ይናገራሉ ፡፡ ይህ በሽታ በብዛት የሚያጠቃው ወንዶችን በተለይም ደግሞ በአመራር ስፍራ ላይ ያሉትን እንደሆነም ይናገራሉ ፡፡ ስለበሽታው ምንነት እና መገለጫዎቹ የኦክስፎርድ ዲክሽነሪ ሲያብራራ እንዲህ ይገልፀዋል ፡ « a personality disorder characterized by an exaggerated sense of self-importance, a need for admiration, and a lack of empathy for other people.» ትርጉሙም ያለልክ የሆነ ወይም የተጋነነ ለራስ የሚሰጥ ቦታ ፣ አድናቆት ፈላጊ እና ለሌሎች ርህራሄን ማጣት በማለት ያስቀምጠዋል ፡፡ በሌላ አነጋገር አፍቅሮተ አምልኮ የተጠናወታቸው ለእግዜር አምስት ጉዳይ ነኝ ነገር መሆን ማለት ነው ፡፡
 
መሪዎችን ማክበር ለእነርሱ የሚገባውን ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ(1ኛ ተሰሎንቄ 5፣12-13) እንደሆነ ባምንም አክብሮቱ በእነርሱና በሚመሩት ህዝብ መካከል ባለ የክርስቶስ ፍቅር እንጂ እነርሱ በተሳሳተ አስተምህሮ እና ማስፈራራት እንዲሁም በግዛታቸው አጥብቀው ስለፈለጉት ስላስተማሩትም መሆን የለበትም ፡፡ (1ኛ ተሰሎንቄ 5፣12-13 ፣1ኛ ጢሞ 5፡17 )
ነገር ግን በዚህ ዘመን ያሉ አንዳንድ መሪዎች ከዚህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ በተቃራኒው ልክፍት የተለከፉ ስለመሆናቸው በአደባባይ የሚናገሩትንና የሚያስተምሩትን መመለከት ብቻ በቂ ነው ፡፡ ሰው በልቡ የሞላውን ይናገራልና !
 
መፅሐፍ ቅዱስ ይህ አይነቱ ችግር መከሰቱ የመጨረሻው ዘመን ምልክት እንደሆነ አጥብቆ ያስተምረናል ፡፡ ከላይ የተገለጡትን የዚህ በሽታ ባህሪያት ጳውሎስ በ2ኛ ጢሞቲዎስ ምዕራፍ 3 ከ ቁጥር 2 ጀምሮ አስተምሮአል ፡፡ «ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉና። ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ። » 2ጢሞቲዎስ ም.3 ቁ 2-5
መሪዎች የሚመሩትን ህዝብ ከእነዚህ የመጨረሻው ዘመን ባህሪያት ቅዱስ ቃሉን በማስተማር እንዲያድኑ ሲጠበቅባቸው እነርሱ በተቃራኒው በእነዚህ ባህሪያት ተለክፈው ማየትም ሆነ መስማት በእጅጉ ያሳዝናል ፡፡
 

የታናሹ ምክር ፤

ለመሪዎች:-
ይህንን ክፉ በሽታ ለማሸነፍ ትልቁ መንገድ መሪዎች እና አገልጋዮች በክርስቶስ በተሰራልን የመስቀል ስራ ፣ክብር፣ ሀይል እና ስልጣን ላይ ማተኮር እንጂ በራሳችን ላይ መሆን የለበትም። ሰውን ሁሉ የሚለውጠውን ፣የሚያድሰውን እና ሀይል ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል ከፍ አድርገን ልናስተምር እና ልንኖር እንጂ ከየትም የለቃቀምነውን ሰዋዊ ጥበብ ማስተማር አይገባንም ፡፡
እንዲሁም ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን እነደተናገረ የሚያጠጣም ቢሆን የሚተክል ምንም እንዳልሆነ በማሰብ እውነተኛ አገልጋይ እንሁን፡፡ ለነገሩ እግዚአብሔር ብቻውን ዘርቶ ፣አጠጥቶ ፣አሳድጎ ያውቃል አሁንም ያሳድጋል ፡፡ ለዚህ ምስክሩ የሙሉ መፅሐፍ ቅዱስ ምልከታ መያዝ በቂ ነው ፡፡
 
ለምእመናን :-
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትንሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኃለሁ ፣ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ ፤
እንዲህ ያሉት ለገዛ ፍቃዳቸው እንጂ ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና በመልካም በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ያታልላሉ ፡፡ ( ሮሜ 16፡17-19 )
አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ ፣እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ (1ጢሞ.2፡5 )
Read 1240 times Last modified on Wednesday, 22 December 2021 15:55
Pastor Fitsum N.Demisse

Youth Pastor @ Bible Army International Church

Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 66 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.