ክርስትና ድሩም ማጉም እምነት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ማመን፤ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፤ በመንፈስ ቅዱስ ማመን፣ በሙታን ትንሣኤ ማመን፣ በክርስቶስ ቤዛዊ ግብር ማመን ወዘተረፈ፡፡ በአጠቃላይ ክርስትና ዋልታና ማገሩ፣ መሠረቱና ውቅሩ እምነት ነው፡፡ የቃሉን ትርጓሜና ዳር ድንበር፣ የመሠረተ ሐሳቡን ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም በርእሰ ጒዳዩ ላይ በሚቀርቡ መስመር የሳቱ ትምህርቶችና ልምምዶች ላይ ሒስ መሰንዘር፣ የዚህ ጽሑፍ መነሻም መድረሻም ነው፡፡ በአጭሩ ጽሑፉ ትምህርታዊና ዐቅብተ እምነታዊ ተልእኮ በመሰነቅ፣ ቃለ እግዚአብሔርንና ምክንዩን የጒዞ መስመሩ ያረገ ጽሑፍ ነው፡፡…