You are here: HomeNews/Eventsየኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝደንት፤ መንፈሳዊ በዓላት ዐቢይ ጭብጣቸውን በሚያንጸባርቅ መንገድ በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ መወሰኑን አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝደንት፤ መንፈሳዊ በዓላት ዐቢይ ጭብጣቸውን በሚያንጸባርቅ መንገድ በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ መወሰኑን አስታወቁ።

Published in News and Events Thursday, 24 March 2016 13:00

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ፣ ትላንት መጋቢት 14 ቀን፣ 2008 .. በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ መንፈሳዊ በዓላት ዐቢይ ጭብጣቸውን በሚያንጸባርቅ መንገድ በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ መወሰኑን አስታወቁ፡፡

 

የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ምድር መምጣት የምናስብበት በዓለ ልደት እንዲሁም የሞቱና የትንሣኤው ድል የእምነታችን ዐበይት አዕማዳት እንደመሆናቸው ስለእነዚህ መንፈሳዊ በዓላት እሴቶች ልንናገር ይገባል” ያሉት ፕሬዝዳንቱ በብሔራዊ ደረጃ እውቅና አግኝተው እየተከበሩ ስላሉት በዓላት “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንዶቻችን ዘንድ አከባበራቸው ልማዳዊ ወደ ሆነ ሥርዓት ወርዶ ዐቢይ የሆነው ትርጉሙ በዘመን ብዛት እየደበዘዘ እንዳይሄድ ከወዲሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወደ ሆነ መስመር መመለስ ግድ ይላል፡፡” በማለት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሥራ አመራር ቦርድ በዓላቱ ዐቢይ ጭብጣቸውን በሚያንጸባርቅ መንገድ በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ ወስኗል፡፡ ይህም ከፊታችን ከሚከበረው የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሳኤ በዓል እንደሚጀምር እና በመላው አገሪቱ በሚገኙ ወንጌላውያን አማኞች ዘንድ በጋራ የሚከበር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

 

በሌላ መግለጫ፡ የኅብረቱ የሥራ አመራር ቦርድ ነቢይቲቢ ጆሽዋ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አገልግሎት መስጠትን በተመለከተ ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ወደ ጽ/ቤቱ ኃላፊነት መመለሱን አስታወቀዋል፡፡

 

ነቢይቲቢ ጆሽዋ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ማገልገልን በተመለከተ የረጅም ጊዜ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ የነቢዩን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ማገልገል የማይደግፉ፣ ከመምጣቱ በፊት ሰፊ ጥናትና የጸሎት ቆይታ ይኑረን ያሉ፣ በሌላ በኩል መምጣቱ ለአገራችን ቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ በመሆኑ የሚደረግለት ጥሪ ይቀጥል ዘንድ ይገባል” የተሰኙ ሐሳቦች በቤተ እምነቶች በኩል በመቅረባቸው እና የኅብረቱ ስራ አመራር ቦርድ ኅብረቱን ከመጠበቅ አንጻር የነቢይ ቲቢ ጆሽዋን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እንደግፋለን ያሉ ቤተ እምነቶች ዝግጅቱን እንዲያካሂዱ ይሁንታውን የሰጠ መሆኑ ይታወሳልሆኖም ፕሮግራሙ በተባለለት ጊዜ ሳይከናወን በመቅረቱ  የኅብረቱ ስራ አመራር ቦርድ የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ባካሄደው 27ኛ ልዩ ስብሰባው “የአጀንዳው ውጪ መቆየት ለኅብረቱም ሆነ ለእርስ በእርስ ግንኙነታችን ክፍተት ሊፈጥር ይችላል ብሎ ስላመነ፣ ኀላፊነቱን ሙሉ በሙሉ ወደ /ቤቱ መልሶ በጕዳዩ ላይ እየተነጋገርንና እየተመካከርን አንድነታችንን በማይጎዳ ሁኔታ መሥመርና አቅጣጫ እናስይዘዋለንየሚል ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡

 

አያይዘውም አገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በማሰብ የአየር ንብረት መዛባት ባስከተለው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ መደፍረስን ተከትሎ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በመመልከትና ወደ እግዚአብሔር ቃል በመመለስ ስለ አገራቸው ሊጸልዩ እንደሚገባ አስታውሰውለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረግንና የአንዳንድ አካባቢዎች ጸጥታ መደፍረስን በሚመለከት ኅብረቱ ምን እያደረገ እንዳለ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ኅብረቱ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጊዜው ሥጋቱን እና የመፍትሔ ሀሳቡን ከማቅረብ እንዳልተቆጠበ ገልጸው በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችም ርዳታ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

Read 12387 times Last modified on Tuesday, 05 April 2016 02:03

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 82 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.