በትላናንትናው ዕለት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ Movement for African National Initiatives (MANI) በሚባል ሚኒስትሪ የተዘጋጀ ስብሰባ “ዛሬ ባለው ሁኔታ እግዚአብሔርን መስማትና መታዘዝ” በሚል መሪ ቃል ተጀምሯል።
የዚህ እንቅስቃሴ ዋና አላማ፥በአፍሪካ ደረጃ ያሉ የቤተክርስቲያናት መሪዎችን ለወንጌል ስራ ለማነቃቃትና ለማጠንከር እንደሆነና ትላንት የተጀመረውም ስብሰባ፥ይህንኑ አላማ ከአለም ዙሪያ በተለይም ከፍሪካ አህጉር ለመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎችና መጋቢዎች ለማካፈል እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።
በስብሰባው ላይ የኢትዮጲያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መሪ ፓስተር ጻድቁ አብዶ ተግኝተው የመክፈቻ ንግግርና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያቀረቡ ሲሆን ፥ የኢትዮጲያ ወንጌላውያን ህብረት ታሪክ የጀመረበትን ጊዜና ሁኔታ በማስታወስ በጊዜው የነበረው የኮሚውኒስት አመራር ብዙ ቤተክርስቲያናትን እንዳዘጋና ይህም ለኢትዮጲያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን ታሪክ ትልቅ ተግዳሮት እንደነበር በማንሳት፥ዛሬ ግን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፥ቤተክርስቲያን በነጻነት እንደተሰፋፋና አምልኮአችንንም በነጻነት የምናደርግበት ለወንጌል አመቺ ጊዜ ላይ እንዳለን ለእንግዶቹ አስታውቀዋል።
ይህ ስብሰባ ሶስተኛው አህጉራዊ የምክክር እንቅስቃሴ ሲሆን፥ ስብሰባውን ለመካፈል ከአለም ዙሪያ የቤተክርስቲያ መሪዎች፥መጋቢዎችና ሚሽነሪዎች ተገኝተዋል።ስብሰባውም ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት በዚሁ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንደሚቀጥል ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።