መግቢያ የክርስቲያን ሐኪሞች እና ዴንቲስቶች ማኅበር - በኢትዮጵያ፣ በአባላቱ መካከል መተናነጽን ለመፍጠር እንዲሁም ለአብያተ ክርስቲያናት እና ለአገር ጠቃሚ ጕዳዮችን ለማበርከት በሚል ዐላማ የተሰባሰቡ የወንጌላውያን ክርስቲያን ሐኪሞችን በማቀፍ ከ30 ዓመታት በፊት የተመሠረተ መንፈሳዊ ማኅበር። ማኅበሩ ከዚህ በፊት የጤና እና የሕክምና ጕዳዮችን በተመለከተ ለአብያተ ክርስቲያናት አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ በተለይ ኤች አይ ቪ - ኤድስ የአገርም ሆነ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ተግዳሮት በነበረበት ወቅት፣ የቅድመ ጋብቻ የኤች አይ ቪ ምርመራ አብያተ…