ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበት ዘመን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ወንጌልን ላልሰሙ ለማሰማት፣ በክርስቲያን ወንድሞች መካከል ያለውንም ፍቅር ለመጠበቅ የተሻለ እድል ያላት ጊዜ ነው። በአንደኛዉ የአለም ጥግ የሚሆን ነገር ጥቂት በሚባሉ ሰከንዶች በሌላኛዉ የአለም ጥግ ይሰማል፤ የዘመኗ ቤተክርስቲያንም ይህንን የቴክኖሎጂ ትሩፋት ለወንጌል ስራ መዋጀትና መጠቀም ይኖርባታል።
በዚህ አቅጣጫ “ቤተክርስቲያንን ማስታጠቅ” (Empowering The Church) በሚል መነሻ ዓላማ የተሰራዉ ሶፍተዌር በኢትዮጵያዊ ወጣት ሮቤል ተሰማ የተሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ቤተክርስትያኖችና ሚኒስትሪዎች አገልግሎት ላይ ይገኛል። ለየትኛዉም የቤተክርስትያን መጠን እና አደረጃጀት እንዲሆን ተደርጎ የተሰራዉ ይህ ሶፍተዌር ቤተክርስትያን የአባሎችዋን መረጃ በተደራጀ መልኩ እንድትይዝ ከማድረጉም ባሻገር ምዕመናንን በየትኛውም ጊዜ ባሉበት ቦታ በሞባይል ስልካቸዉ ከቤተክርስትያን ጋር እንዲገናኙ ያስችላል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሞባይል ስልክ ለብዙ ግልጋሎት መዋል ከመቻሉ ጋር ተያይዞ ከዕለት ዕለት ህይወታችን ጋር ያለው ቁርኝነት እጅጉን መጨመሩ አያጠያይቅም ፤ ምናልባትም አብዛኛውን የዕለት ስራችንን ያለሞባይላችን እገዛ ማከናወን የማይታሰብ የሆነበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ወደ ቤተክርስቲያኖቻችን እንኳ ብንመጣ ሞባይላችን እንደ መጽሐፍ ቅዱሳችን፣ እንደ ማስታወሻችን ብሎም ውስጣችን ያሉ ሃሳቦቻችንን ለሌሎች የምናካፍልበት ምስባክ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው ቤተክርስቲያን በንቃት ይህንን ዕድል መጠቀም ከቻለች ተልዕኮዋን ለመፈጸም ተጨማሪ አቅምን እንደሚፈጥርላት ነው።
ChurchSMS የተባለው ሶፍትዌርም ዋናው ዓላማ ቤተክርስቲያን የሞባይል ስልክ የፈጠረውን ዕድል በቀላሉ መጠቀም እንድትችል ለማስቻልና እያደገ በሚሄደው ቴክኖሎጂ ልክ የቤተክርስቲያን አቅምና ተፅዕኖ እንዲያድግ ማስቻል ነው። ChurchSMS በአሁን ጊዜ ከሚሰጣቸው ዋና አገልግሎቶች መካከል ከታች የተጠቀሱት ሲገኙ በቀጣይነትም ከማህባራዊ መረቦች (Social Networks) ጋር በማስተሳሰር ለቤተክርስቲያን ሁነኛ የመገናኛ መሳሪያ የመሆን ዕቅድ አለው።
የተደራጀ የምዕመናን መረጃ መያዝ
- ግላዊ መረጃ(Personal detail)
- የመገኛ አድራሻ(Contact address)
- መንፈሳዊ ቅድመታሪክ(Church background)
- የቤተሰብ ግንኙነቶች(Family relations)
- የአገልግሎት ዘርፎችና የፀጋ ስጦታዎች(Ministries and Spiritual gifts)
- ለህትመትና ወደ ሌሎች መረጃ ስርዓቶች ለመገልበጥ ዝግጁ የሆነ (Printable and Exportable)
የአጭር ፅሑፍ መልዕክት(SMS) አገልግሎቶች
- የአጭር ፅሑፍ መልዕክቶችን ለአንድ ግለሰብ፣ለቡድን አባላት ወይንም ለአጠቃላይ ምዕመን በአንድ ጊዜ መላክ
- የፀሎት ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን መሰብሰብ
- የፕሮግራም ማስታወሻ ለመላክ(Event Alerts)
- ዕለታዊ ወይንም ሳምንታዊ ጥቅሶችን ለመላክ(Devotional messages)
- ያለሰው እገዛ የሚላኩ ምላሾችን ማበጀት (Auto-Responders) እና ሌሎችም
የአጭር ፅሑፍ መልዕክት አገልግሎት ከሌሎች የመገናኛ መንገዶች በተሻለ በየትኛውም ቦታና ጊዜ የሚሰራ በመሆኑ የኢንተርኔት ሽፋን ዝቅተኛ በሆነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቤተክርስቲያኖችም ጭምር አመቺ የመገናኛ መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። በተጨማሪም የአጭር ፅሑፍ መልዕክት ፈጣን፣ወጪ ቆጣቢና አስተማማኝ የመገናኛ ዘዴ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሊባል በሚቻል ልክ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አባል የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ መሆኑ በራሱ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ዕድል ነው፤ ChurchSMS የተባለው ሶፍትዌርም ቤተክርስቲያን ይህን ዕድል በመጠቀም ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ያግዛታል።
ቤተክርስቲያኖች ይህንን ሶፍትዌር በቀላሉና በአነስተኛ ወጪ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን እንዲህ አይነት ለቤተክርስቲያን ብሎም ለሀገር ፋይዳ ያላቸውን ጅማሬዎች እንድናበረታታ መልእክቴ ነው። ለበለጠ መረጃ www.churchsms.net የሚለውን ድህረገፅ ይጎብኙ።
በኢሜይል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ይፃፉ።
በስልክ ቁጥር +251935932263 ይደውሉ።